ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በብሪክስ የደህንነት ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፤ መስከረም 2/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በሩሲያ ሴንትፒተርስበርግ እየተካሄደ በሚገኘው የብሪክስ የደህንነት ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች ነው።

በስብሰባው የብሪክስ አባል አገራት የደህንነትና የብሔራዊ ደህነንት ጉዳዮች ላይ በመምከር ላይ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያም የባለብዝሃ ወገን የደህንነት ትብብር ላይ ያላትን ተሳትፎ አጠናክራ እንደምትቀጥል ተገልጿል።

የዓለምን የደህንነት ምህዳር ጽንፈኝነት፣ ግጭቶች፣ ሽብርተኝነት፣ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርና ሌሎች ፈተናዎች እየተፈተኑ መሆኑ ተገልጿል።

የስብስባው ተሳታፊዎች የብሪክስ አባል አገራት የደህንነትና የጸጥታ ችግሮችን በመፍታት ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት ያላቸውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል።

የብሪክስ ስብስባ ዛሬ እንደሚጠናቀቅ ኢዜአ ሞስኮ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም