በአሶሳ ከተማ አዲስ ዓመት ማዕድ በማጋራት እየተከበረ ነው

አሶሳ፤ መስከረም 1/2017 (ኢዜአ)፦ በአሶሳ ከተማ የሚገኙ ባለሃብቶች ለአቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ በማጋራት አዲሱን ዓመት እያከበሩት ይገኛሉ።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አብዱልከሪም አብዱራሂም እንደተናገሩት፤ አዲስ ዓመትን ድጋፍ ከሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ማሳለፍ የተለየ ደስታን ይፈጥራል። 

በተለይ በከተማዋ የሚገኙ ባለሃብቶች በበጎ ስራቸው ከመንግስት ጎን በመሆን ለህብረተሰቡ ድጋፍ በማድረግ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን ጠቁመዋል። 


 

መርሃ ግብሩን ያስተባበረው ወጣት እዮብ ዲታሞ በበኩሉ አጋዥ የሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በዓልን በደስታ እንዲያሳልፉ ከማድረግ በላይ ደስታ የለም ብሏል። 

ከማዕድ ማጋራቱ በተጨማሪም የኢኮኖሚ አቅም ለሌላቸው 300 ለሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል።

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም