በቀን አንዴ መመገብ ለማይችሉ ወገኖቻችን 21ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል የአዲስ ዓመት ስጦታ አድርገን እነሆ ብለናል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ - ኢዜአ አማርኛ
በቀን አንዴ መመገብ ለማይችሉ ወገኖቻችን 21ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል የአዲስ ዓመት ስጦታ አድርገን እነሆ ብለናል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2017(ኢዜአ):- በቀን አንዴ እንኳን መመገብ ለማይችሉ ወገኖቻችን 21ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል የአዲስ ዓመት ስጦታችን አድርገን እነሆ ብለናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
በአዲስ ዓመት በቀን 1 ሺህ ሰዎችን የሚመግበውን 21ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አየር ጤና አካባቢ መርቀን በቀን አንዴ እንኳን መመገብ ለሚቸገሩ ወገኖቻችን መልካም አዲስ ዓመት ብለን ምገባ አስጀምረናል ብለዋል።
ከተማችንን ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት ለማድረግ ከጀመርናቸው ስራዎች አንዱ በቀን አንዴ እንኳን መመገብ የሚቸገሩ ወገኖቻችንን መመገብ ሲሆን 21ኛውን የምገባ ማዕከል በረከት ገበሬዋ ገንብታ አስረክባናለች ሲሉም ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።
በቀጣይም ሙሉ ወጪውን ችላ 22ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ገንብታ ለወገኖቿ ለማስረከብ ቃል መግባቷንም ጠቁመዋል።
ለበጎነቷ በተጠቃሚ ነዋሪዎቹ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ላመሰግናት እወዳለሁ ሲሉም አክለዋል በመልዕክታቸው።