ከንቲባ አዳነች አቤቤ 21ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል መርቀው አገልግሎት አስጀመሩ - ኢዜአ አማርኛ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ 21ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል መርቀው አገልግሎት አስጀመሩ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2017(ኢዜአ):- ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ 21ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል መርቀው አገልግሎት አስጀመሩ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በመዲናዋ 21ኛው የምገባ ማዕከል በይፋ ስራ ጀምሯል።
በኮልፌ ክፍለ ከተማ አየር ጤና አካባቢ በበረከት ወርቁ "በበረከት ገበሬዋ" ድጋፍ የተገነባ ሲሆን ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው እለት በይፋ ስራ አስጀምረውታል።
የምገባ ማዕከላቱ በቀን አንድ ጊዜ በራሳቸው መመገብ የማይችሉ ወገኖች የሚመገቡባቸው መሆናቸውን ጠቅሰው ለዚህም የግል ተቋማትና ባለሃብቶች እያደረጉት ላለው እገዛ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ከበረከት ገበሬዋ ጋር በመተባበር አየር ጤና አካባቢ 21ኛውን የተስፋ ብርሀን የምገባ ማዕከል አስገንብቶ ለአገልግሎት አብቅቷል ብለዋል።
ለዚህ በጎ ተግባር በባለሃብቷ ለተደረገው የላቀ አበርክቶም ከንቲባዋ አመስግነዋል።
22ኛውን የተስፋ ብርሀን የመገባ ማዕከል ለመገንባት በአስተዳደሩ በኩል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል።