ቀጥታ፡

በአዲሱ አመት  ለአዳዲስ ውጤቶች ለመብቃት በትጋት እንሰራለን -ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው 

ሆሳዕና ፤ ጳጉሜ 5/2016 (ኢዜአ)፦ በአዲሱ አመት  ለአዳዲስ ውጤቶች ለመብቃት ብርታታችንን፣ ፅናታችንንና ትጋታችንን ከፍ በማድረግ እንሰራለን ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው አስታወቁ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው አዲሱን አመት አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት በአዲሱ ዓመት  አዲስ ተስፋ ሰንቀን፣ አዳዲስ ዕቅዶችን ይዘን ፣ ለአዳዲስ ውጤቶች ለመብቃት ብርታታችንን፣ ፅናታችንን ፣ ትጋታችንን ከፍ በማድረግ እንሰራለን ። 

"እንዲሁም አዲሱ ዓመት እምቅ አቅሞቻችንን እና ፀጋዎቻችንን  አስተባብረን በማንቀሳቀስ አዳዲስ ውጤቶችን እውን ለማድረግ በጋራ የምንተጋበት ዓመት ነው" ብለዋል።

ለዚህም መላው የክልሉ ሕዝቦች የበኩላችውን አስተዋፅኦ ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው አመልክተዋል፡፡ 

"አዲሱ ዓመት በክልላችን በሁሉም መስኮች እመርታ የምናሳይበት፣ በሀሳብና በተግባር ተዋህደን ጠንካራ አንድነት በመፍጠር አዳዲስ ስኬቶችን የምናስመዘግብበት እንዲሆን እመኛለሁ"   ሲሉ ገልፀዋል ። 

ለአዲሱ ዓመት ለ2017 ዓመተ ምህረት፣ የዘመን መለወጫ በዓል እንኳን በሠላም አደረሰን! አደረሳችሁ! በማለት ለመላው ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም ለክልሉ ህዝብ  መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ 

አዲሱ ዓመት የሠላም፣ የአብሮነት፣ የስኬትና የሐሴት እንዲሆንም ተመኝተዋል ።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም