ቀጥታ፡

ጳጉሜ 5 "የነገ ቀን" በተለያዩ ዝግጅቶች በጋምቤላ ከተማ እየተከበረ ነው

ጋምቤላ፤ጳጉሜን 05/2016 (ኢዜአ)፡-ጳጉሜን 5 የነገ ቀን  ‘‘የዛሬ ትጋት፤ ለነገ ትሩፋት’’ በሚል መሪ ሐሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች በጋምቤላ ከተማ እየተከበረ ነው።

የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ አራያት ኡጁሉ በክብረ በዓሉ ላይ እንዳሉት "በዓሉን ስናከበር የነገ ሀገር ተረካቢ ወጣቶችና ህፃናት ሀገራዊ ፍቅር እንዲኖራቸው ለማስቻል ነው"።


 

ሀገርን በከፍታ ማስቀጠል የሚቻለው በእውቀትና በክህሎት የተገነባ፤ የሀገር ፍቅር ያለው ዜጋ ማፍራት ሲቻል በመሆኑ ለትውልድ ግንባታ ትኩረት ሰጥተን ልንሰራ ይገባልም ብለዋል።

ወጣቱ ትውልድ ዘላቂ ለሰላምና ልማትን በማስፋን ረገድም ትልቅ አቅም ያለው በመሆኑ ሁለንተናዊ ተሳትፏችንን አጠናክረን ልንሰራ ይገባል ሲሉም የቢሮ ኃላፊዋ ገልጸዋል።

‘‘የዛሬ ትጋት፤ ለነገ ትሩፋት’’ በሚል መሪ ሐሳብ ጳጉሜ 5 - የነገ ቀን በጋምቤላ ወጣቶችን በሳተፈ መልኩ በፓናል ውይይት፣ በእግር ጉዞ፣ በባህላዊና ዘመናዊ ውዝዋዜዎች እየተከበረ ይገኛል።


 

እንዲሁም ለአቅመ ደካሞች የበዓል መዋያ ስጦታ፣ በትምህርታቸው ውጤታማ ለሆኑ ወጣቶች አጋዥበመለገስ በዓሉ እየተከበረ ነው።

በክብረ በዓሉ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የበጎ ፍቃደኛ አገልግሎት ወጣቶች፣ የወጣት አደረጃጀትና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ ናቸው።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም