ቀጥታ፡

ወጣቱ ነገ የሚረከባትን ሀገር ሰላሟን ለማስጠበቅና ልማቷን ለማስቀጠል የሚጠበቅበትን መወጣት እንዳለበት ተገለጸ

ሀዋሳ ፣ ጳጉሜ 5/2016 (ኢዜአ)፦ ወጣቱ የነገው ቀን የሱ መሆኑን ተረድቶ ነገ የሚረከባትን ሀገር ሰላሟን ለማስጠበቅና ልማቷን ለማስቀጠል የሚጠበቅበትን መወጣት እንዳለበት ተገለጸ።

ጳጉሜ 5 የነገው ቀን "ለኑሮ ምቹ፣ ጽዱና ውብ ከተማ ለነገው መደመር ትውልድ እናሻግራለን" በሚል መሪ ሀሳብ በሲዳማ ክልል ደረጃ በሀዋሳ እየተከበረ ነው።


 

የክልሉ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ደስታ ለገሰ እንዳሉት 'የነገ ቀን' በተለያዩ መርሃ ግብሮች እየተከበረ ነው።

በመሆኑም የክልሉ ወጣት 'የነገ ቀን' የእሱ መሆኑን ተረድቶ ነገ የሚረከባትን ሀገር ሰላሟን ለማስጠበቅና ልማቷን ለማስቀጠል የሚጠበቅበትን መወጣት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የክልሉ ወጣቶች ሀገርን ሰላም ለማድረግና ነገ ብሩህ ተሰፋ እንዲኖር የሚያስችል ጉዳይ ላይ ማተኮር እንዳለባቸውም አመልክተዋል።

ቀኑ በሀዋሳ ከተማ በእግር ጉዞና በፓናል ውይይት እየተከበረ ሲሆን በስነ-ስርዓቱ ላይ ከሀዋሳ ከተማ ሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ወጣቶች ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ የቢሮ አመራር አባላትና ሰራተኞች እንዲሁም ወጣቶች ተገኝተዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም