ቀጥታ፡

ጳጉሜን 5 " የነገ ቀን" በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች በመከበር ላይ ነው

ሠመራ፤ ጳጉሜን 5/2016 (ኢዜአ)፦ የጳጉሜን 5 " የነገ ቀን" በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች በመከበር ላይ ነው።

"የዛሬ ትጋት፤ ለነገ ትሩፋት" በሚል መሪ ሐሳብ የተዘጋጀው የጳጉሜን መጨረሻ ቀን የአዲሱ ዓመት ዋዜማ በዓል በአፋር ክልል ሠመራ ከተማ በልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች በመከበር ላይ ነው።

በበዓሉ የፖሊስ ማርሽ ባንድ፣ የእግር ጉዞና ሌሎች የጎዳና ላይ ትእይንቶች የታዩ ሲሆን፤ ቀጥሎም የፓናል ውይይት እንደሚኖር ከወጣው መርሃግብር ለመረዳት ተችሏል።

የዕለቱን መርሃ ግብር ያዘጋጁት የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ፣ የክልሉ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ፣ የክልሉ ባህል፣ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ እና የሠመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር በጋራ በመሆን ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም