በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጳጉሜን 5 ''የነገ ቀን'' በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጳጉሜን 5 ''የነገ ቀን'' በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው
ሶዶ፣ ጳጉሜ 5/2016(ኢዜአ)፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጳጉሜን 5 'የነገ ቀን' ''የዛሬ ትጋት፤ ለነገ ትሩፋት" በሚል መርህ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው።
በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከበረው የጳጉሜ 5 'የነገ ቀን' "የዛሬ ትጋት፤ ለነገ ትሩፋት" በሚል መሪ ሀሳብ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።
ቀኑ ከማለዳው ጀምሮ በእግር ጉዞ መከበር የጀመረው ዕለቱ ፥ የተለያዩ መልዕክቶችም እየተላለፉበት ነው።
በመርሃ ግብሩ ላይ የክልሉና የዞኑ ከፍተኛ አመራር አባላት፣የወጣት አደረጃጀቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ህጻናት፣ ተማሪዎችና የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች እየተሳተፉ ነው።