በሐረሪ ክልል "የነገ ቀን" በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በሐረሪ ክልል "የነገ ቀን" በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው
ሐረር፤ ጳጉሜን 5/2016 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል "የነገ ቀን" በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው።
“የዛሬ ትጋት፣ ለነገ ትሩፋት" በሚል መሪ ሐሳብ በጀጎል ዓለም አቀፍ ቅርስ ዙሪያ በሚገኘው ኑር ፕላዛ የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር በመዘመር ነው ቀኑ መከበር የጀመረው።
እንዲሁም በተማሪዎች የተሰሩ የፈጠራ ስራዎች ዐውደ ርዕይ በእንግዶቹ ተከፍቶ ለእይታ በቅቷል።
በስነ ስርዓቱም በብልጽግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ አብዱልሃኪም ኡመር፣ የክልሉ ከፍተኛና በየደረጃው የሚገኙ የአመራር አካላት፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ ተማሪዎችና ሌሎች ተሳትፈዋል።
እለቱን በማስመልከት በከተማው በሚገኘው አሚር አብዱላሂ የመሰብሰቢያ አደራሽ የተለያዩ ሁነቶች ይካሄዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።