የነገው ትውልድ እጅግ የተሻለች ኢትዮጵያን እንደሚረከብ ርግጠኞች ነን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ጳጉሜን 5/2016(ኢዜአ)፦የነገው ትውልድ እጅግ የተሻለች ኢትዮጵያን እንደሚረከብ ርግጠኞች ነን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የዛሬ ትጋት ለነገ ትሩፈት ነው! በሚል ሀሳብ የሚከበረውን የጳጉሜን 5 ቀን አስመልክተው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልክታቸውም ትናንት አልቋል። ዛሬም እየተገባደደ ነው። ነገ ግን ገና አልተነካም። ነገን ለመጠቀም ታድያ ዛሬ መሥራት አለብን ብለዋል።

ሕዳሴ ግድብ፤ የገበታ ለሀገርና የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች፤ መንገዶችና ግድቦች፤ የተቋም ግንባታ ሥራዎች፤ አረንጓዴ ዐሻራና ኢትዮጵያ ታምርት፤ የኮሪደር ልማትና የሌማት ትሩፋት ፤ ዲጂታል ኢትዮጵያ እና የትምህርት ቤት ምገባ፤ ሀገራዊ ምክክርና የሽግግር ፍትሕ፤ ሌሎችም.. ነገን የተሻለ ለማድረግ የምንሠራቸው ናቸው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ፤ ለነገ ዛሬ እየሠራን ነውና ፥ የነገው ትውልድ እጅግ የተሻለች ኢትዮጵያን እንደሚረከብ ርግጠኞች ነን ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም