ጳጉሜ-4 “የኅብር ቀን" ዶሃ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተከበረ - ኢዜአ አማርኛ
ጳጉሜ-4 “የኅብር ቀን" ዶሃ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተከበረ
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2016(ኢዜአ)፦ጳጉሜ-4 “የኅብር ቀን" በሚል ስያሜ “ኅብራችን ለሰላማችን" በሚል መሪ ኃሳብ በካታር ዶሃ ዛሬ ተከብሯል።
የኢትዮጵያዊያንን ብዝሀ ቋንቋ፣ ባህል፣ ታሪክ፣ እምነት፣ ማኅበራዊ መስተጋብር በሚያንጸበርቅ መልኩ በዓሉ መከበሩም ተገልጿል።
ኅብረ ብሔራዊ ማንነታችን ውበታችን እንዲሁም ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን ደግሞ ለሰላማችን መሰረት መሆኑን በማሰብ ተከብሯል ሲል ኤምባሲው በማህበራዊ ትስስር ገጹ ያሰፈረው መረጃ ያመለክታል።
በበዓሉ ላይም ዲፕሎማቶች፣ ሰራተኞች እና ኢትዮጵያውያን መሳተፋቸውም ተገልጿል።