ጳጉሜ - 4 የኅብር ቀን ፤ የኢትዮጵያዊያንን ውብ ኅብረ ብሔራዊ እሴት በሚያጎሉ ዝግጅቶች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ጳጉሜ - 4 የኅብር ቀን ፤ የኢትዮጵያዊያንን ውብ ኅብረ ብሔራዊ እሴት በሚያጎሉ ዝግጅቶች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2016(ኢዜአ)፦ የኅብር ቀን የተሰየመችው ጳጉሜን-4 “ኅብራችን ለሰላማችን" በሚል መሪ ኃሳብ የኢትዮጵያዊያንን ኅብረ ብሔራዊ እሴት በሚያጎሉ ዝግጅቶች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር በድምቀት እየተከበረ ነው።
የ2017 ዓ.ም የአዲስ ዓመት ዋዜማ አምስቱ የጳጉሜን ቀናት "የመሻገር፣ የሪፎርም፣ የሉዓላዊነት፣ የኅብር እና የነገ" በሚሉት ዐበይት የቀናት ሥያሜ በአገር አቀፍ ደረጃ በድምቀት መከበር ከጀመረ አራተኛ ቀኑን ይዟል።
በዚህም የመሻገር ቀን የሆነችው ጳጉሜን-1 “የመሻገር ጥሪቶች፤ የአዲስ ብርሃን ወረቶች"፣ በሪፎርም ቀን የተሰየመችው ጳጉሜን-2 “ሪፎርም ለላቀ አገልግሎት"፣ ጳጉሜን-3 ደግሞ የሉዓላዊነት ቀን በሚል ስያሜ “ኅብር ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት" በሚሉት መሪ ኃሳቦች በአገር አቀፍ ደረጃ በድምቀት በመከበር ላይ ይገኛሉ።
በዛሬው ዕለትም ከማለዳው ጀምሮ በአገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረች የምትገኘው የኅብር ቀን በሚል ሥያሜ የተሰየመችው ጳጉሜን-4 “ኅብራችን ለሰላማችን" በሚል መሪ ኃሳብ በአዲስ አበባ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር የኢትዮጵያዊያንን ኅብረ ብሔራዊ ድምቀት በሚያሳይ የመድረክ ትዕይንት በድምቀት እየተከበረ ነው።
በክብረ በዓል ዝግጅቱ ላይም በባህል ቡድኖች አማካኝነት የኢትዮጵያዊያን ኅብረ ብሔራዊ ውበት የሚታይበት የመድረክ ላይ ትዕይንት ቀርቧል።
በመርኃ ግብሩ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የኃይማኖት አባቶች የአገር ሽማግሌዎች፣ የባህል ቡድን አባላትና ሌሎች አካላት ተገኝተዋል።