ቀጥታ፡

ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከጅቡቲ የንግድና የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፤ ጳጉሜን 4/2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከጅቡቲ የንግድና የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር ዮኒስ አሊ ጉዌዲ ጋር ተወያይተዋል።

ኢንጂነር ታከለ ሚኒስትር ጉዌዲ የባቡር መስመሩን ከስትራቴጂካዊ ወደቦች ጋር በማስተሳሰር ቀጣናዊ ንግድን ለማሳለጥ እያደረጉት ያለው ያላሰለሰ ጥረትና አመራር ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ይህም የሁለቱን አገራት ኢኮኖሚ እድገት የሚጨምርና ትብብራቸውን የሚያጠናክር መሆኑን ዋና ስራ አስፈጻሚው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

ኢንጂነር ታከለ ሚኒስትሩ የኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር አገልግሎት የኃይል መቆራረጥ እንዳያጋጥመው ላደረጉት ድጋፍም አመስግነዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም