የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሐመድ በሰራዊቱ በጋምቤላ ክልል እየተከናወነ ያለውን የግብርና ልማት ለመጎብኘት ጋምቤላ ገብተዋል - ኢዜአ አማርኛ
የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሐመድ በሰራዊቱ በጋምቤላ ክልል እየተከናወነ ያለውን የግብርና ልማት ለመጎብኘት ጋምቤላ ገብተዋል
ጋምቤላ፤ ጳጉሜን 04/2016 (ኢዜአ)፡-የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሀመድ በሰራዊቱ በጋምቤላ ክልል እየተከናወነ ያለውን የግብርና ልማት ለመጎብኘት ዛሬ ጋምቤላ ገብተዋል።
ኢንጅነር አይሻ ጋምቤላ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ዓለሚቱ ኡሞድና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋልዋክ ሮን(ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ሚኒስትሯ በሚኖራቸው ቆይታ በኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የዳሎል ማዕካላዊ ዕዝና በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን በጋምቤላ ክልል እየተካሄደ ያለውን የግብርና ልማት ስራዎችን ተዟዙረው ይመለከታሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ጳጉሜን 4 - የኅብር ቀን “ኅብራችን ለሰላማችን” በሚል መሪ ቃል በመላ ሀገሪቷ በማስ ስፖርትና በሌሎች መርሃ ግብሮች እየተከበረ ይገኛል።