ቀጥታ፡

ኅብረ ብሔራዊነታችን መልካችን፣ አንድነታችን ደግሞ ህልውናችን ነው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2016 (ኢዜአ)፦ ኅብረ ብሔራዊነታችን መልካችን፣ አንድነታችን ደግሞ ህልውናችን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ የብዙ ብሔሮች፣ የብዙ ቋንቋዎች፣ የብዙ ባህሎች፣የብዙ እምነቶች፣ የብዙ ሥልጣኔዎች፣ የብዙ ጀግኖች፣ ሀገር ናት። ኢትዮጵያ ኅብር ናት ሲሉ ገልጸዋል።

ሁሉም የኛ በእኛ ለእኛ የተሰጡ ናቸው። ሁሉን እናከብራለን፤ በሁሉም እንኮራለን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመልዕክታቸው።


 

ኅብረ ብሔራዊነታችን መልካችን፣ አንድነታችን ደግሞ ህልውናችን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እነዚህ ኅብራዊ ጸጋዎች በአንዲት ሀገር በኢትዮጵያ የሚገኙ ናቸውም ብለዋል።

ዓላማችን አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ መገንባት ነው። ግባችን የኢትዮጵያ ብልጽግና ነው። ይህ ነው አንድነታችን ሲሉም አክለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተበታተንን ኅብሮች አይደለንም፤ የተጨፈለቅን አንድ ዓይነቶችም አይደለንም። እኛ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ያለን ኢትዮጵያውያን ነን ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም