ጳጉሜን 3 የሉዓላዊነት ቀን በደብረ ብርሀን ከተማ ተከበረ - ኢዜአ አማርኛ
ጳጉሜን 3 የሉዓላዊነት ቀን በደብረ ብርሀን ከተማ ተከበረ
ደብረ ብርሀን፤ ጳጉሜን 3/2016 (ኢዜአ) ፡- " ኅብር ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት" በሚል መሪ ሀሳብ የሉዓላዊነት ቀን ዛሬ በደብረ ብርሃን ከተማ ተከበረ።
በሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል አበባው ሰይድ ፣
የሰሜን ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ተክለየስ በለጠ እና የደብረ ብርሀን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት ዕለቱን አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል።
የመከላከያ ሰራዊትና የፌዴራል ፖሊስን ጨምሮ ሌሎች የፀጥታ አባላትና በየደረጃው የሚገኙ አመራር አባላት በበዓሉ አከባበር ሥነ-ሥርዓት ተሳታፊ ሆነዋል።
የሉዓላዊነት ቀን በዓል በለውጡ ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የተገዳደሩ ፈተናዎችን በመቋቋም የአገርን አንድነትና ሉዓላዊነት ለማፅናት የተከናወኑ ሥራዎችን በማሰብ ዛሬ በአገር ደረጃ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።