ቀጥታ፡

የአገር ሉዓላዊነትን በማስከበር ብልፅግናን ለማረጋገጥ  ከመቼውም ጊዜ በላይ መትጋት አለብን- ርዕሰ መስተዳድር  አረጋ ከበደ  

ባህር ዳር፤  ጳጉሜን  3/ 2016(ኢዜአ)፡-የአገር ሉዓላዊነትን በማስከበር  የኢኮኖሚ እድገትና  ብልፅግናን ለማረጋገጥ   ከመቼውም ጊዜ በላይ መትጋት አለብን ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር  አረጋ ከበደ ገለጹ።

 "ህብር ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት" በሚል መሪ የሉዓላዊነት ቀን በባህር ዳር ከተማ  በፓናል ውይይት መከበር ጀምሯል።   

በሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ባደረጉት ንግግር ፤ ጀግኖች አባቶቻችን በደምና አጥንታቸው መስዋትነት በመክፈል ሉዓላዊነቷ የተከበረች አገር አስረክበውናል ሲሉ  አውስተዋል። 

ከአባቶቹ የወረስነውን ጀግንነት በመላበስ የአገራችንን ሉዓላዊነት በማስክበር  ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ መትጋት አለብን ብለዋል።

ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገትን አስቀጥሎ ብልፅግናን ለማረጋገጥ  መስራት እንደሚገባም አመልክተዋል። 


 

የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር በመዘመር የተጀመረው የሉዓላዊነት ቀን በፓናል ውይይት እየተከበረ ሲሆን፤  በበዓሉም በሉዓላዊነት ማስከበርና ሰላም ማስፈን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ተቋማት እውቅና እንደሚሰጣቸው ተመልከቷል።

በብልፅግና ፓርቲ የአማራ ክልል ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይና የክልሉ   ፖሊስ ኮሚሽነር ደስየ ደጀን፣ የመከላከያ ሰራዊትና የፖሊስን  ጨምሮ  ሌሎችም የፌደራልና የክልሉ  አመራር አባላት በበዓሉ አከባበር ሥነ-ሥርዓት ላይ  ታድመዋል።

በአገር ደረጃ የሉአላዊነት ቀን በዓል በለውጥ ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የተገዳደሩ ፈተናዎችን በመቋቋም የአገርን አንድነትና ሉዓላዊነት ለማፅናት የተከናወኑ  ሥራዎችን በማሰብ በመከበር ላይ ይገኛል።

ዛሬ ከቀኑ 6፤00 ሰዓት ላይ ደግሞ  የመንግሥትና በግል ተቋማት ሰንደቅ ዓላማ በመስቀል ሁሉም ሰው ባለበት ቆሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር የሚዘምርበት ሥነ-ሥርዓት እንደሚኖር ታውቋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም