የሉዓላዊነት ቀን በአዳማ ከተማ በመከበር ላይ ይገኛል - ኢዜአ አማርኛ
የሉዓላዊነት ቀን በአዳማ ከተማ በመከበር ላይ ይገኛል
አዳማ ፤ ጳጉሜን 3/2016(ኢዜአ)፡- " የሉዓላዊነት ቀን ህብር ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት" በሚል መሪ ሀሳብ በአዳማ ከተማ በመከበር ላይ ይገኛል ።
ቀኑ እየተከበረ ያለው በለውጥ ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የተገዳደሩ ፈተናዎችን በመቋቋም የአገርን አንድነትና ሉዓላዊነት ለማፅናት የተሰሩ ሥራዎችን በማሰብ ነው ።
በአዳማ ከተማ ቀኑ በተለያዩ ወታደራዊ የሰልፍ ትርዒት እየተከበረ ነው።
በመረሃ ግብሩ ላይ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ፣ ፌዴራል ፖሊስና የክልሉ ፖሊስ አባላት በሰልፍ ትርዒቱ ተሳታፊ ሆኖዋል።
የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ሰዓዳ አብዱራሃማን፣ ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ ኢሊያስ ዑመታ፣ የክልሉ የፀጥታ ክላስተር አመራር አባላት በተገኙበት በደማቅ ስነ ስርዓት እየተከበረ ይገኛል
በአገር አቀፍ ደረጃ ዛሬ ከቀኑ 6፤00 ሰዓት ላይ የመንግሥትና በግል ተቋማት ሰንደቅ ዓላማ በመስቀል ሁሉም ሰው ባለበት ቆሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር የሚዘምርበት ሥነ-ሥርዓት እንደሚኖር ቀደም ብሎ ተገልጿል።