ቀጥታ፡

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የ3ኛው አየር ምድብ ያስገነባቸውን የውጊያና ሌሎች መሠረተ ልማቶች መርቀው ከፈቱ

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 2/2016(ኢዜአ)፦ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የአየር ኃይል የ3ኛው አየር ምድብ ያስገነባቸውን የተለያዩ የውጊያና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን መርቀው ከፍተዋል።


 

በምርቃቱ ላይ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ፣ የአየር ኃይል አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳና የድሬደዋ ከተማ አስተዳድር ከንቲባ ከድር ጁሀር ተገኝተዋል።

ኢታማዦር ሹሙ በአየር ምድቡ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን የጎበኙ ሲሆን ያለበትን የዝግጁነት ደረጃ መመልከታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም