የጋምቤላ ክልል መንግስት አዲስ የካቢኔ አባላትን ይፋ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
የጋምቤላ ክልል መንግስት አዲስ የካቢኔ አባላትን ይፋ አደረገ
ጋምቤላ፤ ጳጉሜን 2/2016(ኢዜአ)፦ የጋምቤላ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ዓለሚቱ ኡሞድ አዲስ የካቢኔ አባላትን ይፋ አደረጉ።
በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ዓለሚቱ ኡሞድ ዛሬ አዲሱን የካቢኔ መዋቅር አስመልክተው ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።
ወይዘሮ ዓለሚቱ በመግለጫቸውም በክልሉ አሁን ላይ የተገኘውን ሰላም በማስቀጠል የልማት ስራዎችን ለማፋጠን ካቢኔውን በአዲስ መልክ ማዋቅር ማስፈለጉን ተናግረዋል።
በዚሁ መሰረት፦
1. ዶክተር አቤል አሰፋ - የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ
2. አቶ ፓል ቱት - የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ኃላፊ
3. አቶ ኡኩኝ ኦኬሎ - የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ
4. ኡጁሉ ኡዶል - የውሃና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ
5. ወይዘሮ አራያት ኡጁሉ - ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
6. አቶ ዶል ኡኩሪ - የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ
7. አቶ ኮንግ ኩላንግ - የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ
8. ዶክተር ዴቪድ ሯች - ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ
9. አቶ አምቢሳ ያደረታ - የአካበቢ ጥበቀና አየር ንብርት ለውጥ ቢሮ ኃላፊ
10. አቶ ሯች ባየክ - የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ
11. ወይዘሮ ኛሞች ጊል - የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ
12. አቶ ቸንኮት ዴቪድ - የገቢዎች ቢሮ ኃለፊ
13. አቶ ሙሴ ጋጀት - የመስኖና ቆላማ አካባቢ ቢሮ ኃላፊ
14. አቶ ማህበር ኮር - የክለሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ
15. ዶክተር ኡማን አሙሉ - የክልሉ ፋየናንስ ቢሮ ኃላፈ
16. አቶ ላክደር ላክባክ - ፐብሊክ ሰውሀብትና ልማት ቢሮ ኃለፊ
17. ወይዘሮ ክርሚስ ሌሮ - የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ቢሮ ኃለፊ
18. አቶ ጁል ናንጋል - የባህልና ቱሪም ቢሮ ሆነው መሸማቸውን ገልጸዋል።
የተሰጠው ሹመት የትምህርት ዝግጅትን፣ የስራ ልማድን፣ የብሄር ስብጥርንና በማህበረሰቡ ዘንድ ያላቸውን ተቀባይነት መሰረት ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
አዲሶቹ የካቢኔ አባላት ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን በመዋጋት የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ምላሽ የመስጠት አቅም እንዳላቸውም ርዕሰ መስተዳድሯ ገልጸዋል።