ቀጥታ፡

የምስራቅ ዕዝ የሰራዊት አባላት በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ

ሐረር ፤ ጳጉሜን 2/2016(ኢዜአ)፦ የምስራቅ ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ወገኖች የአምስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ።

የምስራቅ ዕዝ የሰራዊት አባላት ድጋፉን ያደረጉት ዛሬ የዕዙ 47ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በሐረር ኢማም አህመድ ስታድየም በተከበረበት ወቅት ነው። 

የዕዙ የሰራዊት አባላት የገንዘብ ድጋፉን ያደረጉት ከኪሳቸው በማዋጣት መሆኑም በእለቱ ተገልጿል። 

ድጋፉም በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ወገኖች እንደሚውልም ተመላክቷል። 

"የምስራቁ ጮራ የኢትዮጵያ ወታደሮች ነን" በሚል መሪ ሃሳብ የምስራቅ ዕዝ 47ኛ ዓመት ምስረታ የማጠቃለያ ክብረ በዓል በሐረር ከተማ በድምቀት ተከብሯል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም