ቀጥታ፡

የሪፎርም ስራዎችን ከሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት በተጨማሪ በሁሉም ተቋሞቻችን ላይ በከፍተኛ ተነሳሽነት በመስራት ላይ እንገኛለን - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 2/2016(ኢዜአ)፦ የሪፎርም ስራዎችን ከሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት በተጨማሪ በሁሉም ተቋሞቻችን ላይ በከፍተኛ ተነሳሽነት በመስራት ላይ እንገኛለን ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ::

ዛሬ ጷጉሜን 2 የሪፎርም ቀን ሪፎርም ለላቀ አገልግሎት በሚል መሪ ሀሳብ በመላ ሀገሪቱ እየተከበረ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት የዲጂታላይዜሽን ስራ ተመርቆ ስራ ጀምሯል::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ቀኑን በማስመልከት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የሪፎርም ስራዎችን ከሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት በተጨማሪ በሁሉም ተቋሞቻችን ላይ በከፍተኛ ተነሳሽነት በመስራት ላይ እንገኛለን ብለዋል::

በሪፎርም ጀምረን ትልቅ ውጤት ካስመዘገብንባቸው ስራዎች አንዱ የሆነው እና ለረዥም ጊዜያት የህዝባችን የቅሬታ ምንጭ የነበረው የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት በ119 ወረዳዎች ዲጂታላዝ አድርገን የዜጎቻችንን እንግልት መቀነስ የሚያስችል ደረጃ ላይ በማምጣታችን በጣም ደስ ብሎናል ሲሉም ገልጸዋል::


 

የሪፎርማችን ውጤታማነት የሚለካው ለህዝባችን ፍትሀዊ አገልግሎት በመስጠት በመሆኑ አገልግሎትን የሚያቀላጥፍ እና የህዝቡን እንግልት የሚቀንስ የሪፎርም ስራዎችን ከሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት በተጨማሪ በሁሉም ተቋሞቻችን ላይ በከፍተኛ ተነሳሽነት በመስራት ላይ እንገኛለን ብለዋል በመልዕክታቸው::

ዛሬ ያስመረቅነው የዲጂታላይዜሽን ስራ ከዋና መስርያ ቤት እስከ ወረዳ ያለውን የቴክኖሎጂ መስመር በአዲስ አሰራር የቀየረ፣ 119ኙም የተቋሙ ጽህፈት ቤቶች የአገልግሎት አሰጣጥ በቀጥታ በካሜራ ቁጥጥር የሚደረግበት (Command Center)ያቀፈ፣ በአይነቱ በሃገራችን የመጀመርያ የሆኑ የዘርፉ መፍትሄዎችን የያዘ እንዲሁም በከተማችን የሚሰጠውን አገልግሎት ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረ ነው ሲሉም አክለዋል ከንቲባዋ::

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም