የምስራቅ ዕዝ 47ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በሐረር ኢማም አህመድ ስታድየም እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የምስራቅ ዕዝ 47ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በሐረር ኢማም አህመድ ስታድየም እየተከበረ ነው
ሐረር ፤ ዻጉሜ 2/2016 (ኢዜአ)፡- በሀገር መከላከያ ሰራዊት የምስራቅ ዕዝ 47ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የማጠቃለያ መርሃ ግብር በሐረር ኢማም አህመድ ስታድየም በድምቀት እየተከበረ ነው።
የምስራቅ ዕዝ 47ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ከነሐሴ 21 ቀን 2016 ዓም ጀምሮ በሐረሪ ክልል እና ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተሞች ሲከበር ሰንብቷል።
በዓሉም የልማት ስራዎችን በመጎብኘት፣ ሙዝየምና የፎቶ ግራፍ ዓውደ ርዕይ ለእይታ በማቅረብ፣ የፕሮጀክት ስራዎችን በመመረቅ ሲከበር ቆይቷል።
የምስራቅ ዕዝን ተጋድሎና ታሪክ የያዘ መጽሃፍ ለንባብ በማብቃት፣ ዘጋቢ ፊልምና ሙዚቃዎችን ለእይታ በማቅረብና በሌሎች ፕሮግራሞችም ክብረ በዓሉ ሲከናወን ዛሬ ላይ ደርሷል።
"የምስራቁ ጮራ የኢትዮጵያ ወታደሮች ነን" በሚል መሪ ሃሳብ የዕዙ 47ኛ ዓመት ምስረታ የማጠቃለያ ክብረ በዓል በሐረር ኢማም አህመድ ስታድየም በድምቀት እየተከበረ ነው።
በስነ ስርዓቱ ላይ የጦር ሃይሎችኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ፣ የአየር ሃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ፣ ከፍተኛ የጦር ጄኔራሎችና መኮንኖች ተገኝተዋል።
እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር፣ የሐረሪ ክልልና የምስራቅ ሐረርጌ ዞን አመራሮች፣ አባ ገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች የክልሉና የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ማህበረሰብና ሌሎች እንግዶች በስታድየሙ ተገኝተዋል።