ቀጥታ፡

ሀገርን በትክክለኛው መንገድ ላይ ለማራመድ ተከታታይና ውጤታማ ሪፎርሞች ያስፈልጉናል -ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 2/2016 (ኢዜአ):- ሀገርን በትክክለኛው መንገድ ላይ ለማራመድ ተከታታይና ውጤታማ ሪፎርሞች ያስፈልጉናል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የአስተሳሰብ፣ የአኗኗር፣ የአሠራርና የአመራረት ሪፎርሞች። በለውጡ ዘመን የተለያዩ ሪፎርሞችን አሳክተናል ብለዋል።

የጸጥታ ተቋማት፣ የፍትሕ ዘርፍ፣ የግብርና፣ የአምራች ዘርፍ፣ የትምህርት ፣ የሲቪል ሰርቪስ፣ የዲጂታል ዘርፍ፣ የውጭ ግንኙነትና የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሞች በትግበራ ላይ ናቸው ሲሉም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ብልጽግና የእነዚህ ድምር ውጤት ነው ሲሉም አመላክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም