ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ከሳዑዲ አረቢያ ጋር ያላትን ወዳጅነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በትኩረት ትሰራለች - አምባሳደር ጣፋ ቱሉ

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 1/2016(ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ ከሳዑዲ አረቢያ ጋር ያላትን ወዳጅነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በትኩረት እንደምትሰራ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስል ጀነራል አምባሳደር ጣፋ ቱሉ ገለጹ።

አምባሳደር ጣፋ የሹመት ደብዳቤአቸውን በሳውዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካ ግዛት ዳይሬክተር ጀነራል ለማዜን አል ሃምሊ አቅርበዋል።


 

ኢትዮጵያና ሳዑዲ አረቢያ ወዳጅነት ዘመናትን የተሻገረና ጥልቅ ትስስር እንዳላቸው ገልጸው የታሪክ የባህልና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ የዚሁ ማሳያ መሆኑን አምባሳደሩ አንስተዋል።

ኢትዮጵያ ይህን ወዳጅነት በተለያዩ ዘርፎችም ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በትኩረት እንደምትሰራ አመልክተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካ ግዛት ዳይሬክተር ጀነራል ማዜን አል ሃምሊ አምባሳደሩ የሁለቱን አገራት ግንኙነት የማጠናከር ተልዕኳቸው እንዲሳካ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ መግለጻቸውን በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም