ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአሜሪካው ኤቪዳይን ኤሮሰርቪስ ኩባንያ ጋር በትብብር መስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 1/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአሜሪካው የአቪዬሽን ጥገና አገልግሎት ሰጪ ኩባንያ ኤቪዳይን ኤሮሰርቪስ ኩባንያ ጋር በትብብር መስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።

የመግባቢያ ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት ያላቸውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት የሚያጠናክርና በአቪዬሽኑ ዘርፍ የላቀ ደረጃ ለመድረስ ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን አየር መንገዱ ገልጿል።

በስምምነቱ አማካኝነት ተቋማቱ በአቪዬሽን ስልጠናና ጥገና አገልግሎቶች ያላቸውን የትብብር አድማስ ለማስፋት እንደሚሰሩ ተመላክቷል።

ይህም ለኢኖቬሽንና የላቀ አገልግሎት ለማቅረብ በር የሚከፍት መሆኑን ነው አየር መንገዱ ያስታወቀው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም