ቀጥታ፡

የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመጪው ትውልድ ለማውረስ እንትጋ-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 1/2016(ኢዜአ)፦ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመጪው ትውልድ ለማውረስ እንትጋ'' ሲሉ የጳጉሜን አዲስ ቀንን ተቀብለዋል።አክለውም ''የመሻገር ጥሪቶች፤ የአዲስ ብርሃን ወረቶች'' ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብልጽግና የሚረጋገጠው በብርቱ ሥራ ነው። ከሠራነው ያልሰራነው፤ ከመጣንበት የምንሄድበት ጉዞ ይበልጣል ብለዋል።

ስለዚህም ሰዓት፣ ቀን፣ ሳምንት፣ ወርና ዓመት የሚባሉ የጊዜ መክፈያዎች ሁሉ ለሥራ መዋል አለባቸው ነው ያሉት። የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመጪው ትውልድ ለማውረስ እንትጋ ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም