ቀጥታ፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ተጠናቀቀ

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 30/2016 (ኢዜአ)፡-  የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሲያካሂድ የቆየውን የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ዛሬ ማጠናቀቁን አስታወቀ። 

የክልሉን ማህበረሰብ አጀንዳ ለማደራጀት የተመረጡ የህብረተሰብ ተወካዮችና ባለድርሻ አካላት በክልሉ የተነሱ አጀንዳዎችን ለኮሚሽኑ አስረክበዋል።

የምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶክተር ዮናስ አዳዬ አጀንዳውን በተረከቡበት ወቅት እንደገለጹት፤ ምክክር ሁሉም አሸናፊ የሚሆንበት ነው።


 

ለሁለንተናዊ ችግሮቻችን ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት ምክክር ወሳኝ መፍትሔ ስለመሆኑም ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ በክልሉ ህዝብ የተነሱ አጀንዳዎችን መረከቡን ገልጸዋል።

ለዚህም ስኬት ሙሉ ጊዜያቸውን በመስጠት አጀንዳዎችን በማሰባሰብና በማደራጀት ለምክክር ኮሚሽኑ በማስረከብ ለተሳተፉ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል።

ኮሚሽኑ ከነሐሴ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በክልሉ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ወኪሎች ጋር ሲያካሂደው የቆየው የምክክር መድረክ ዛሬ ማጠናቀቁንም አስታውቀዋል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም