የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ መዋለንዋያቸውን ቢያፈሱ መንግሥት አስተማማኝ እገዛና ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነው- አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 30/2016(ኢዜአ)፦የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ መዋለንዋያቸውን ቢያፈሱ መንግሥት አስተማማኝ እገዛና ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ።

ከ450 በላይ የቻይና ኩባንያዎች የተሳተፉበት የኢትዮ-ቻይና የቢዝነስ ፎረም በቻይና ቤጂንግ ሚኒስትሮች በኢፌዲሪ ኤምባሲ አዘጋጅነት ተካሂዷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በቢዝነስ ፎረሙ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር በኢትዮጵያና ቻይና መካከል ያለው ግንኙነት የላቀ ደረጃ ላይ መድረሱን ገልጸዋል።


 

በዚሁ እንዳሉት የቻይና ኩባንያዎች በተጠናከረ ደረጃ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ እንዲሠማሩ አምባሳደሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ይህን ዕድል በመጠቀምም የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ መዋለንዋያቸውን ቢያፈሱ መንግሥት አስተማማኝ እገዛና ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

በፈረሙ ላይ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ፣ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዶ/ር ዘለቀ ተመስገን በየዘረፉ ያለውን የኢንቨስትመንት ዕድሎችና አስቻይ ምቹ ሁኔታዎችን የሚያስገነዝቡ ገለጻዎችን አድርገዋል።

ሚኒስትሮቹ የቻይና ባለሀብቶች ምቹ ሁኔታዎችን በመጠቀም መዋለ ንዋያቸውን በኢትዮጵያ እንዲያፈሱና የሁለቱን አገራት ግንኙነት በኢኮኖሚ ትስስር የበለጠ እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም