ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቻይና-አፍሪካ ጉባኤ መክፈቻ ሥነሥርዓትን ተካፈሉ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቻይና-አፍሪካ ጉባኤ መክፈቻ ሥነሥርዓትን ተካፈሉ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 30/2016(ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቻይና-አፍሪካ ጉባኤ መክፈቻ ሥነሥርዓትን መካፈላቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
ቻይና ከአፍሪካ ጋር ላላት ትብብር አስር ዘርፎችን ይፋ አድርጋለች።
ከነዚህም ንግድ፣ ኢንደስትሪ ፣ ጤና፣ ግብርና፣ መገናኛ አውታሮች ልማት፣ አረንጓዴ ልማት እና ደኅንነት ይገኙበታል። እነዚህ መስኮች ኢትዮጵያ ከትብብር ማእቀፉ እንድትጠቀም የሚያስችሉ ናቸው።