ጀኔራል አበባው ታደሰ በ47ኛው የምስራቅ ዕዝ በዓል ለመታደም ጅጅጋ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
ጀኔራል አበባው ታደሰ በ47ኛው የምስራቅ ዕዝ በዓል ለመታደም ጅጅጋ ገቡ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 30/2016 (ኢዜአ)፡- የጦር ሀይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው ታደሰ 47ኛውን የምስራቅ ዕዝ የምስረታ ክብር በዓል ለመታደም ጅግጅጋ ገብተዋል።
ጀኔራል አበባው ጅግጅጋ ሲደርሱ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድን ጨምሮ ከፍተኛ የሠራዊቱና የክልሉ አመራሮች ተገኝተዋል።
በዕዙ 47ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓል ላይ ለመታደም ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል አመራሮች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።