ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከታንዛንያ ጋር አቻ ተለያየች

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከታንዛንያ አቻው ጋር ባደረገው የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታ ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይቷል።

ብሔራዊ ቡድኑ ሁለተኛና የሜዳ ጨዋታውን ጳጉሜ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ዳሬ ሰላም በሚገኘው ቤንጃሚን ምካፓ ስታዲየም (የታንዛንያ ብሔራዊ ስታዲየም) ያከናውናል።

ኢትዮጵያ ባለችበት ምድብ 8 የሚገኙት ጊኒና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አርብ ጳጉሜ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ኪንሻሳ ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

በሞሮኮ አስተናጋጅነት በሚካሄደው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ 48 አገራት በ12 ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም