የቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና የፋይናንስ አካታችነት ስራዎችን እንደሚደግፍ ገለጸ - ኢዜአ አማርኛ
የቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና የፋይናንስ አካታችነት ስራዎችን እንደሚደግፍ ገለጸ
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ፤28/2016 (ኢዜአ)፡- የቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ኢትዮጵያ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ፋይናንስ አካታችነት ዘርፎች እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን እንደሚደግፍ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱና የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዮዳሄ ዘሚካኤል ከቢልና ጌትስ ፋውንዴሽን የጋራ መስራችና ባለቤት ቢል ጌትስ ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ ኢትዮጵያና ፋውንዴሽኑ በዲጂታል ፋይናንስ አካታችነት በተለይም ቀጣናዊ፣ የስርዓተ ጾታና ሌሎች የፋይናንስ አማራጮች ተደራሽነት ያለውን ትብብር ማጠናከር ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።
የቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን የኢትዮጵያ መንግስት የዲጂታል መሰረተ ልማቶችንና የዲጂታል አገልገሎቶችን ለማስፋት እያከናወናቸው ያሉ ስራዎችን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቋል።
በዲጂታል መሰረተ ልማት የዲጂታል ሽግግርን እውን በማድረግ የፋይናንስ አካታችነትን ለማሳለጥ ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።