ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ የሚያደርገውን በረራ አቋረጠ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 27/ 2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ የሚያደርገውን በረራ ከነገ ጀምሮ እንደሚያቋርጥ አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ በረራውን ያቋረጠው በኤርትራ ውስጥ አገልግሎቱን ለመስጠት ባጋጠመው አስቸጋሪ ሁኔታ መሆኑን ገልጿል።

ከነገ ነሐሴ 28 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮም ወደ ኤርትራ መዲና አስመራ ሲያደርግ የነበረውን በረራ እንደሚያቋርጥ ከአየር መንገዱ ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም