አትሌት ያየሽ ጌቴ በፓራሊምፒክ ጨዋታዎች ለኢትዮጵያ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኘች - ኢዜአ አማርኛ
አትሌት ያየሽ ጌቴ በፓራሊምፒክ ጨዋታዎች ለኢትዮጵያ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኘች
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 27/2016(ኢዜአ):- በ17ኛው የፓራሊምፒክ ጨዋታዎች አትሌት ያየሽ ጌቴ በ1500 ሜትር ሴቶች የአይነ ስውር(T-11) ፍጻሜ በማሸነፍ ለኢትዮጵያ በውድድሩ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች።
አትሌት ያየሽ 4 ደቂቃ ከ27 ሴኮንድ ከ68 ማይክሮ ሴኮንድ በራሷ ተይዞ የነበረውን የዓለም ክብረ ወሰን በአራት ሴኮንድ በማሻሻል አንደኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።