ታማኙ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ባለሙያ በስራው ቦታ ላይ ወድቆ ያገኘውን 7 ሺህ ዶላር አስረከበ - ኢዜአ አማርኛ
ታማኙ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ባለሙያ በስራው ቦታ ላይ ወድቆ ያገኘውን 7 ሺህ ዶላር አስረከበ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 26/2016(ኢዜአ)፦ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ባለሙያ የሆነው አሸናፊ ወንዲራድ በስራ ቦታ ወድቆ ያገኘውን 7 ሺህ ዶላር አስረከበ።
አቶ አሸናፊ በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የኬላዎች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት የቦሌ አየር ኬላ ሠራተኛ ሲሆን በቀን 25/12/2016 ዓ.ም ቦሌ አየር ኬላ በወጪ መንገደኞች ማስተናገጃ ካውንተር ተመድቦ በስራ ላይ እያለ በስራ አካባቢው ከነቦርሳው ያገኘውን ሰባት ሺህ የአሜሪካ ዶላር አስረክቧል።
ታማኙ ባለሙያ ወድቆ ያገኘውን ገንዘብ ለቅርብ ሃላፊው በማሳወቅና በጋራ በመቁጠር በኤርፖርቱ ውስጥ በሚገኘው የጠፉ እቃዎች ማቆያ ክፍል በማስረከብ ለሁሉም የዶላር ኖት ቁጥር በማስመዝገብ ደረሠኝ በመቀበል አርዓያነት ያለውና ታማኝነቱን የሚያሣይ ተግባር መፈጸሙን ከአገልግሎቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።