የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ዳካ ከተማ በሳምንት ስድስት ቀናት አዲስ በረራ ይጀምራል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ዳካ ከተማ በሳምንት ስድስት ቀናት አዲስ በረራ ይጀምራል
አዲስ አበባ ፤ነሐሴ 24/2016(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ አየር መንገድ የባንግላዴሽ ዋና ከተማ ወደሆነችው ዳካ ከተማ ከጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሳምንት ስድስት ቀናት አዲስ በረራ እንደሚጀምር አስታወቀ።
ይህ አዲስ የበረራ መስመር የኢትዮጵያ አየር መንገድ በደቡብ እስያ ያለውን ተደራሽነት የሚያሰፋ መሆኑን አየር መንገዱ ገልጿል።
እንዲሁም በባንግላዴሽ እና አፍሪካ መካከል ብሎም ከተቀረው ዓለም ጋር የሚደረገውን ግንኙነት ይበልጥ እንደሚያጠናክር ከአየር መንገዱ የተገኘው መረጃ ያመልክታል።