የግብርና ሚኒስትር ዶክተር ግርማ አመንቴና ሌሎች ከፍተኛ አመራር አባላት በዱብቲ ወረዳ ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

ሰመራ፤ ነሐሴ 24/2016(ኢዜአ)፡- የግብርና ሚኒስትር ዶክተር ግርማ አመንቴና ሌሎች ከፍተኛ አመራር አባላት በአፋር ክልል ዱብቲ ወረዳ አይሮላፍና ገበላይቶ ቀበሌ ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ።


 

በመርሃ ግብሩ ላይ ከግብርና ሚኒስትሩ በተጨማሪ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የተጠሪ ተቋማት ዳይሬክተሮችና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

እንዲሁም በአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አሊ መሀመድን፣ የክልሉ ግብርና ቢሮ አመራር አባላትና ሰራተኞችም በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ ተሳትፈዋል።

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም