ቀጥታ፡

ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 23/2016(ኢዜአ)፦የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ነሐኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ከኢትዮጵያ አንጋፋ ምሁራን አንዱ የሆኑትና በተለያዩ ሀላፊነቶች ሀገራቸውን ያገለገሉት ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ በተማሪዎች ንቅናቄ ንቁ ተሳትፏቸው እና በብሄር መብት ተሟጋችነታቸው ይታወቃሉ።

ከኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት ዘመን ጀምሮ ሕገ መንግስት በማርቀቅና በማማከር ከፍተኛ ተሳትፎ ያደረጉት ፕሮፌሰር አንድርያስ፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ፕሬዝዳንት ሆነው ከማገልገላቸው በተጨማሪ በተለያዩ የመንግሥት ሀላፊነቶች ሀገራቸውን አገልግለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በፕሮፈሰሩ ሕልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለጸ፤ ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም