ቀጥታ፡

የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ከዓለም የምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 23/2016(ኢዜአ)፦ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ(ዶ/ር) አዲስ የተሾሙትን የዓለም የምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዝላታን ሚሊሲችን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሁለቱ ወገኖች የዜጎቹን የኑሮ ሁኔታ በሚለውጡ ፕሮጀክቶች፣ በዘላቂ የአነስተኛ መስኖ ልማትና ገበያን መሰረት ባደረጉ የመስኖ ልማት መርሐ ግብሮች ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን ከመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም