ቀጥታ፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ አገር አቀፍ የንግድ ሣምንት ኤግዚቢሽንን ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 22/2016(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር "የኢትዮጵያን ይግዙ ''በሚል መሪ ኃሳብ ያዘጋጀው የንግድ ሣምንት ኤግዚብሽንን ጎበኙ። 

ከንቲባ አዳነች  ከኤግዚብሽኑ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ማሳያ ማዕከልንም ተዘዋውረው  የጎበኙ ሲሆን ገለጻና ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።  

ኤግዚብሺኑ ገዥና ሻጩን ማገናኘት፣ በዘርፉ ያለውን አቅም ማስተዋወቅ እንዲሁም በንግድና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ነው።    

ኤግዚቢሽኑ  ከነሐሴ 19 እስከ 23 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን በነገው ዕለት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።   

በንግድ ሣምንቱ ከኤግዚብሽኑ ጎን ለጎን የፓናል ውይይትን ጨምሮ  የተለያዩ  መርኃ ግብሮች  መካሄዱን ተገልጿል። 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም