ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ቦይንግ እና ቲንክ ያንግ ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች በሳይንስ፣ቴክኖሎጂ፣ምህንድስናና ሒሳብ ትምህርቶች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመረቁ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 22/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ቦይንግ እና ቲንክ ያንግ በቅንጅት ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ለተውጣጡ ተማሪዎች በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሒሳብ ትምህርቶች (STEM)ያሳለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመርቀዋል።

ሰልጣኞቹ ከ28 የተለያዩ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሆኑ ስልጠናውም በኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቪርሲቲ በኩል መሰጠቱ ተገልጿል።

የስልጠና ፕሮግራሙ ለሁለተኛ ጊዜ የተሰጠ ሲሆን የትምህርት ተደራሽነት በበቂ ሁኔታ ባልተሟላባቸው አካባቢዎች ላሉ ወጣቶች ልዩ ትኩረት ያደርጋል ተብሏል።

በዚህ በ2ኛው ዙር ከተመረቁ ተማሪዎች ውስጥ 50 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም