የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ “World Travel Awards” ሽልማት በስድስት ዘርፎች ዕጩ ሆኖ ቀርቧል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ “World Travel Awards” ሽልማት በስድስት ዘርፎች ዕጩ ሆኖ ቀርቧል
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 22/2016(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2024 “World Travel Awards” ሽልማት በስድስት ዘርፎች ዕጩ ሆኖ ቀርቧል።
ዘርፎቹ ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ፣ ምርጥ የአፍሪካ ቢዝነስ ክላስ አየር መንገድ፣ ምርጥ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ክላስ አየር መንገድ፣ ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ ብራንድ፣ ምርጥ የአፍሪካ የበረራ ላይ መዝናኛ መፅሔት (ሰላምታ መጽሄት) እና ምርጥ የአፍሪካ ኮንፈረንስ ሆቴል (የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል) ናቸው።
ዜጎች በተቀመጠው https://www.worldtravelawards.com/vote-r3#votenow ሊንክ በመጠቀም ድምጽ እንዲሰጡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጥሪውን አቅርቧል።
የድምጽ አሰጣጡ እስከ ጳጉሜን 3 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆይ መሆኑም ተገልጿል።
እርስዎም ከላይ በተቀመጠው ሊንክ https://www.worldtravelawards.com/vote-r3#votenow በመግባት የሃገር ኩራት ለሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ድምጽዎን ይስጡ።