ቀጥታ፡

በትግራይ ክልል የስምንተኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

መቀሌ፤ ነሀሴ 22/2016(ኢዜአ)፡- በትግራይ ክልል የስምንተኛ ክፍል ክልል አቀፍ  ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ፡፡

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ  ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዶክተር ታደሰ ካህሳይ ለኢዜአ እንደገለጹት በ2016 የትምህርት ዘመን 114ሺህ 600 የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና ወስደዋል።

ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 96 በመቶ ያህሉ ማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ተናግረዋል።

በክልሉ በ2016 የትምህርት ዘመን 1ሺህ 129 የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ማስፈተናቸውን አስታውቀዋል ።

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም