ቀጥታ፡

"የኢትዮጵያን ይግዙ ''በሚል መሪ ኃሳብ የተዘጋጀው የንግድ ሣምንት ዛሬም ቀጥሏል

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 22/2016 (ኢዜአ)፦የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር "የኢትዮጵያን ይግዙ ''በሚል መሪ ኃሳብ ያዘጋጀው የንግድ ሣምንት ዛሬ ሦስተኛ ቀኑን ይዟል።

በዚህም የጥራት መሰረተ ልማት ላይ ያተኮረ የፓናል ወይይት እየተካሄደ ነው።


 

በፓናል ውይይቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው፣ የሚኒስቴሩ ተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች እንዲሁም የንግድ ማኅበረሰብ አባላት ተገኝተዋል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ያስቻለ ነው።


 

ጎን ለጎንም ጥራትን ለማስጠበቅም የተለያዩ ተግባራት መከናወኑን ጠቅሰው በተለይም የጥራት ቁጥጥር የመሰረተ ልማት ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን አንስተዋል።

የኢትዮጵያን የወጪ ገቢ ንግድ ሚዛን ለማስጠበቅ ጥራት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

በመሆኑም አምራቾች የምርትና አገልግሎት ጥራት ላይ አተኩረው መሥራት እንዲሁም ሸማቹም የአገር ውስጥ ምርት የመጠቀም ባህልን ማሳደግ እንዳለበት ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም