ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሲዳማ ክልል አጀንዳ ለማሰባሰብ ያዘጋጀው መድረክ በሐዋሳ ተጀመረ

ሐዋሳ ፤ ነሐሴ 22/2016(ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሲዳማ ክልል አጀንዳ ለማሰባሰብ ያዘጋጀው መድረክ  ዛሬ በሐዋሳ ከተማ ማካሄድ ጀመረ።

በመድረኩ ላይ ከክልሉ 45 ወረዳዎች የተወከሉ 1 ሺህ 800 የማህበረሰብ ክፍሎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የተለያዩ ተቋማት ተወካዮች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተወካዮችና ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እየተሳተፉ ነው።


 

መርሃ ግብሩ ለአንድ ሳምንት የሚካሄድ ሲሆን የማህረሰብ ክፍሎቹ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ሀገራዊ መግባባት የሚፈጥሩ አጀንዳዎቻቸውን በህዝባዊ ውይይት የሚሰበስቡበት ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ዛሬ በተጀመረው መድረክ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽነሮች የአጀንዳ ልየታን አስመልክተው ገለጻ ካደረጉ በኋላ የማህበረሰቡ  ተወካዮች  በቡድን በቡድን ሆነው ውይይት ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም