ለ24 ሺህ የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞች አዳዲስ የሪፎርም እሳቤዎችን የተመለከተ ስልጠና ነገ ይጀመራል - ኢዜአ አማርኛ
ለ24 ሺህ የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞች አዳዲስ የሪፎርም እሳቤዎችን የተመለከተ ስልጠና ነገ ይጀመራል
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 21/2016(ኢዜአ)፦ በዘርፉ ያሉ አዳዲስ የሪፎርም እሳቤዎች ላይ ያተኮረ አገር አቀፍ ስልጠና ለ24 ሺህ የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞች ከነገ ጀምሮ እንደሚሰጥ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ።
ስልጠናው "ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት" በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄድ ነው።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ ስልጠናው በዘርፉ ያሉ አዳዲስ የሪፎርም እሳቤዎችን ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸዋል።
በአገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው ስልጠና 24 ሺህ ሰልጣኞች እንደሚሳተፉና ከነሐሴ 22 እስከ ጳጉሜን 3/2016 በ17 ማዕከላት በሁሉም ክልሎች እንደሚሰጥ ተናግረዋል።
ስልጠናው ተወዳዳሪ ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚያስችል የሰው ኃይል ለማፍራት ያለመ መሆኑንም ጠቁመዋል።