በክልሉ ጽንፈኝነትን እንደሚቃወሙና የመንግስትን ህግ የማስከበር ተግባር እንደሚደግፉ የከሚሴ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች በሰላማዊ ሰልፍ እየገለጹ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በክልሉ ጽንፈኝነትን እንደሚቃወሙና የመንግስትን ህግ የማስከበር ተግባር እንደሚደግፉ የከሚሴ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች በሰላማዊ ሰልፍ እየገለጹ ነው

ከሚሴ ፤ ነሐሴ 21/2016 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ጽንፈኝነትንና ህገ ወጥ ድርጊትን እንደሚቃወሙና የመንግስት ህግ የማስከበሩን ተግባር እንደሚደግፉ የከሚሴ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች በሰላማዊ ሰልፍ እየገለጹ ነው ።
በሰላማዊ ሰልፉ የከተማውና አካባቢው ነዋሪዎች ጽንፈኝነትንና ህገ ወጥ ድርጊትን የሚቃወሙ መልዕክቶችን እያስተላለፉ ይገኛሉ።
ሰልፈኞች "ያለ ሰላም ልማት የለም፣ ህገ ወጥ የመሳሪያ ዝውውር ይቁም፣ ከመሪዎቻችን ጎን እንቆማለን፣ አንድነታችንን ጠብቀን ለሰላማችን ዘብ እንቆማለን" የሚሉት እያስተላለፉት ካሉት መልዕክቶች መካከል ይገኙበታል።
እንዲሁም በአማራ ክልል የቀድሞው ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳዳሪ ገዳዮች ለህግ ይቅረቡ፣ የህግ የበላይነት ይከበር፣ ጽንፈኝነትን እንቃወማለን ሲሉም ገልጸዋል።
ከሰልፉ አስተባባሪዎች መካከል አቶ ሰይድ አሊ በሰጡት አስተያየት ፤ ህብረተሰቡ የዞኑን ልማት፣ ህግ ማስከበርና የሰላም ስራ ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት ለማሳየት በሰላማዊ ሰልፍ ድጋፉን እያሳየ ነው ብለዋል።
በሰልፉ ከከሚሴ ከተማ ነዋሪዎች በተጨማሪ የአጎራባች ወረዳዎችና ከተሞች ነዋሪዎች እየተሳተፉ እንደሚገኙም ተናግረዋል።