50 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ከጅቡቲ ወደ ተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የማጓጓዝ ስራ ተጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
50 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ከጅቡቲ ወደ ተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የማጓጓዝ ስራ ተጀመረ
አዲስ አበባ ፤ነሐሴ 20/2016(ኢዜአ)፦ 50 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ከጅቡቲ ወደ ተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የማጓጓዝ ስራ ዛሬ መጀመሩን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ።
የምግብ ዘይት ስርጭቱ መንግስት ገበያን ለማረጋጋት እየወሰደ የሚገኘው ተከታታይነት ያለው እርምጃ አካል መሆኑን አመልክተዋል።
የምግብ ዘይቱ በኢትዮ-ጅቡቲ ባቡርና በጭነት ተሽከርካሪዎች ወደ ኢትዮጵያ እየገባ እንደሆነም ተጠቁሟል።
የፍጆታ ዕቃው በዋነኝነት አቅርቦቱን ለማሳደግና ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት ታስቦ በመንግስት ግዢ የተፈፀመ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።